Google Toneን እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

Google Toneን በመጠቀም ዩአርኤል ለማሰራጨት፦

  • ወደ የእርስዎ Google መለያ ይግቡ።
  • ለማሰራጨት በሚፈልጉት የድር ገጽ ላይ እንዳሉ በእርስዎ የChrome አሳሽ ውስጥ  የGoogle Tone አዶን ጠቅ ያድርጉ።

ለምን Google Tone ያስፈልጋል?

Google Tone ኮምፒውተሮች ልክ እኛ እንደምናደርገው—እርስ በራሳቸው በመነጋገር መልዕክት እንዲለዋወጡ ያስችላል። ልዩ የድምጽ ፊርማን እንዲያወጡ ለሌሎች የኮምፒውተሮች ማይክራፎኖች እንደ ዩአርኤል ለይተው እንዲያውቁ Chrome የእርስዎን ኮምፒውተር ስፒከሮች እንዲጠቀም የሚያስችል የአሳሽ ቅጥያ ነው።

Google Tone እንዴት ይሰራል?

Google Tone የእርስዎን ኮምፒውተር ማይክሮፎን ያበራል (ቅጥያው በሚበራበት ጊዜ)። Google Tone በጊዜያዊነት ዩአርኤልን በGoogle አገልጋዮች ላይ ያስቀምጣል እና ወደ በአቅራቢያ ያሉ ከበይነበረመረብ ጋር የተገናኙ ኮምፒውተሮች ይህንን ለመላክ የእርስዎን ኮምፒውተር ስፒከሮች እና ማይክራፎን ይጠቀማል። በጆሮ ማዳመጥ በሚቻልበት ክልል ውስጥ ያለ እና የGoogle Tone ቅጥያ የተጫነበት እና የበራለት ማናቸውም ኮምፒውተር የGoogle Tone ማሳወቂያን ይቀበላል። ማሳወቂያው ከእርስዎ የGoogle መገለጫ ስም እና ስዕል ጋር ዩአርኤሉን ያሳያል።

የGoogle Tone ዩአርኤል ለመቀበል፣ Chrome የእርስዎን ማይክራፎን እንደበራ ማቆየት ይፈልጋል። Google Tone ከፍተኛ ጩኸት ባለባቸው ቦታዎች፣ ከርቀት ላይ፣ከደካማ የበይነመረብ ግንኙነት፣ ወይም ማይክራፎን ከሌላቸው ኮምፒውተሮች ጋር ወይም በGoogle Tone የሚሰራጭ ድምጽን ፈልጎ ለማግኘት ከማይችል ማይክራፎን ጋር ላይሰራ ይችላል።

Google Tone የእኔን ውሂብ እንዴት ይጠቀማል?

Google Tone የማን እንደሆነ የማይታወቅ የአጠቃቀም ውሂብ በGoogle የግላዊነት መመሪያ መሰረት ይሰበስባል።

እንዴት አበራዋለሁ እና አጠፋዋለሁ?

(ማይክራፎኑን ጨምሮ) Google Toneን ለማብራት እና ለማጥፋት ወደ የChrome ቅጥያ ቅንብሮች ይሂዱ።

ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

Google Tone ዩአርኤሎችን ብቻ ስለሚያሰራጭ ተቀባዮች በተራው ሁኔታ መዳረሻ ሊኖራቸው ወደማይችል ገጽ መዳረሻን በራስ-ሰር ሊያገኙ አይችሉም። የእርስዎን የGmail ገቢ መልዕክት ሳጥን ዩአርኤል ለምሳሌ ካሰራጩ በGoogle Tone ማሳወቂያ ላይ ጠቅ የሚያደርጉ ተቀባዮች ወደ የእነርሱ Gmail በመለያ እንዲገቡ ይጠየቃል። ሆኖም ግን፣ Google Tone ስርጭቶች በዲዛይናቸው የወል ስለሆኑ ምስጢራዊ መረጃን ለመለዋወጥ አለመጠቀም ከምንም በላይ የሚመረጥ ነው።